Telegram Group & Telegram Channel
አሜሪካ በኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ መብጠልጠል የፈለገችበት ምክንያት ምንድነው?

እርግጥ ነው አሜሪካ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የመላው አገራት ጠላት እንደሆነች ይታወቃል:: ከራሱዋ ውጭ የሌላውን አገር ሰላምና እድገት ፈልጋ አታውቅም ልትፈልግም አትችልም:: አሜሪካን የሚያውቅ ሁሉ ይህን እውነት ያውቃል:: በዚህ አመሉዋ መጠላትም መወገዝም ያለባት አገር ልትሆን ትችላለች::
ነገር ግን ሰሞነኛው የኢትዮጵያ መንግስት ከመጠን ያለፈው ጫጫታ ዛቻና ማስፈራሪያ ከአሜሪካ ክፋት ጋር የተያያዘ አይመስልም!

የአሜሪካ ሪዞሉሽን እና የኢትዮጵያ መንግስት ምላሽ ጨርሶ የሚመጣጠን አይደለም:: ይህ ቁጣና ማስፈራሪያ ዛቻ እና ስድብ አልፎም ባንዲራዋን የማቃጠል ጭምጭምታ ከአሜሪካ ፍላጎት የመነጨና በአሜሪካ መንግስት ግፊት እየሆነ ያለ እስካልሆነ ድረስ የሃገራችን መንግስት በራሱ ንዴትና ብስጭት ተነሳስቶ እየሄደበት ያለ አካሄድ ሊሆን አይችልም!

ምክንያቱም አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ጣለች የተባለው ማዕቀብ ሴክሽን 212 a የሚባለውን ነው:: ይህ ደግሞ በዋናነት በተራ የቪዛ ክልከላ የተወሰነ የማንንም ባለስልጣን ስም የማይጠቅስ እንዲሁ "ወደ አገሬ ላትገቡ ትችላላችሁ" የሚል ተራ ማስፈራሪያና ማስጠንቀቂያ ብቻ ነው::

ጩኸቱ ዛቻና ማስፈራሪያው ወይም ከኢትዮጵያ በኩል የተሰጠው ምላሽ ግን ለዚህ ሴክሽን ሳይሆን ሴክሽን 730 c ለተባለው ለእውነተኛው ማዕቀብ እንኩዋን የማይመጥን አደገኛ የሚባል ምላሽ ነው::
ምናልባት የማዕቀቡ ወሬ ይህ 730 c የተባለው ሴክሽን ቢሆን ከባድ የሆነ የሰብዓዊ መብት ጥሰትና ከፍተኛ ምዝበራን የሚመለከት ነውና በተራ የቪዛ ማስፈራሪያ ሳይወሰን የባለስልጣናቱን ስም እስከፈጸሙት ወንጀል በግልጽ ዘርዝሮ የሚያስቀምጥ, በጉዞ ዕቀባ ሳይወሰን መንግስትን እንደ መንግስት በዓለም አቀፍ ወንጀል የሚያስከስስ ከጠቅላይ ሚ/ሩ ጀምሮ ያሉትን አመራሮች ለፍርድ እንዲቀርቡ የሚያደርግ የእስር ማዘዣ የሚያስወጣ የኢኮኖሚ ማዕቀብን የሚያካትት ወዘተ...የእውነት ማዕቀብ ነውና ሊያስቆጣ ሊያንጫጫ ይችላል::

የማዕቀቡ ወሬ ለጊዜው ይህን ሴክሽን የሚመለከት አይደለም:: ሪዞሉሽኑ ለምንም አይነት ጫጫታ የማይዳርገው ሴክሽን 212 a የተባለው ነው:: ይህ ደግሞ "ማዕቀብ" ተብሎ ሊጠቀስም ሊገለጽም የማይችል ነው::
ይህ ባይሆንና እውነተኛው ማዕቀብ ተጣለ ብለን ብናስብ እንኩዋን በዚህ ደረጃ አይደለም ለአሜሪካ መልስ የሚሰጠው:: እንደ መንግስት ስድብም ከሆነ ዲፕሎማሲያዊ ስድብ ነው::
ትችትም ከሆነ ዲፕሎማሲያዊ ትችት ነው የሚቀድመው:: "እረፊ ጣልቃ አትግቢብን" ከሆነም እንደ መንግስት ለስለስ ብሎ አቅምን አውቆ ነው ተገቢ ምላሽ የሚሰጠው::እየሆነ ያለው ግን ሌላ ተዓምር ነው!

የአሜሪካ ሴራ እየታወቀ፤ ከፍለህ የማትጨርሰው የአሜሪካ እዳ እያለብህ፤ ከሱዳን ጋር የመዋጋት አቅም የለንም እያልክ በግልጽ በምትናገርበት አንደበትህ የአሜሪካን ባንዲራን እስከማቃጠል የደረሰ አመጽ ውስጥ እንዲገባ በመንግስት ደረጃ ግፊት ማድረግ... ግልጽ የሆነ የ "ነይና አተራምሽን" ጥሪ ተብሎ ሊወሰድ የሚችል ነው::

እንደ ሩሲያ ያሉ በጦር ኃይልም በኢኮኖሚም አሜሪካን መገዳደር የሚችሉ ኅያል አገራት እንኩዋን አሜሪካ ያሻትን ብትል ያሻትን አይነት ማዕቀብ ብትጥል በዚህ ደረጃ መልስ አይሰጡም::
እንዲህ ያለው የተጋነነ ምላሽ ከሊቢያም ከኢራቅም ከኢራንም ከዙምባብየም ከማናቸውም ማዕቀብ ከተጣለባቸው አገራት በኩል ተሰንዝሮ አያውቅም::
ጭራሽ የዛሬዋ ኢትዮጵያ ደግሞ አይደለም ከአሜሪካ ጋር የኢትዮጵያን ግዛት በወረራ በያዘችውና 80 ኪ.ሜ ድረስ ዘልቃ ገብታ የራሱዋን መንገድ ሆስፒታልና ድልድይ እየገነባች ያለችውን ሱዳን ማስወጣት ባቃተው ግድየለሽ መንግስት እየተመራች ያለች አገር ናት!

እውነት አሜሪካን መስደብ መቆጣትና ማስፈራራት ካስፈለገም ወቅቱ አሁን አይደለም:: ይህ ወቅት የግብጽ የጦር ጉሰማ ያለበት፤ ሱዳን ሃያል ሆና ኢትዮጵያን በሃይል የወረረችበት፤ ከ 5 ሚሊዮን በላይ የትግራይና የአማራ ህዝቦች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በየመጠለያ ጣቢያው በየት/ቤቱ ተጠልለው የሚገኙበት ክፉ ውቅት ላይ ነን::

ይህ በሆነበት ሁኔታ ነው ኢትዮጵያ አሜሪካን "ጸብ ያለሽ በዳቦ" እያለቻት የምትገኘው::
ለጊዜው ይህ ነው የሚባል ጫና የሚያሳድር ሉዓላዊነትን የሚገዳደር ማዕቀብ አልተጣለም! በኢትዮጵያ መንግስት በኩል እየሆነ ያለው ግን እንደተባለው ሌላ ተዓምር ነው! እየተሰጠ ያለው አላስፈላጊና አቅምን ያላገናዘበ ድፍረት የተሞላበት ምላሽ ከዚህ ተራ ሴክሽን ጋር የሚመጣጠን ምላሽ አይደለም:: መንግስታዊ የቃላት ሽንቆጣው አገሪቱ ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታ ያገናዘበ አይደለም::

በጥቅሉ አሜሪካን በሚመለከት የአሜሪካ መንግስት ካወጣው መግለጫ ወይም ሊያደርግ ካሰበው የቪዛ እቀባ ማስጠንቀቂያ ይልቅ ከኢትዮጵያ መንግስት የተሰጠው ምላሽ አስደንጋጭ ሆኖ ይገኛል::
ይህ ደግሞ ከመሬት ተነስቶ የሚመጣ ድፍረት አይደለም::

እንዲህ እንዲያደርጉ በራሱዋ በአሜሪካ ካልተፈቀደላቸው ወይም በራሱዋ በአሜሪካ ካልታዘዙ በቀር በዚህ አጣብቂኝ ወቅት ይህን ወደመሰለ ድፍረት ሊያልፉ የሚችሉበት ምክንያት ሊኖር አይችልም::
ለአሜሪካ እየተሰጡ ያሉት ምላሾችም ከጤናማ የአገር ፍቅር ስሜትና ከሉዓላዊነት ቁጭት የመነጩ አይደሉም:: ስለዚህ ቁም ነገሩ ያለው የኢትዮጵያ መንግስት እንዴት ይህን ለማለት ደፈረ? የሚለው ላይ ሳይሆን:- አሜሪካ ይህ አይነቱ መልዕክት እና ስድብ ከኢትዮጵያ በኩል ደምቆ እንዲቀነቀን የፈለገችበት ምክንያት ምንድነው? የሚለው ነው! በኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ መሰደብ መብጠልጠል የፈለገችበት ምክንያት ምንድነው? የሚለውን ነጥብ መረዳት ሲቻል ብቻ ነው አሜሪካ ወደ ቀጣዩ ዕቅዱዋ ልትሸጋገር እየተንደረደረች እንዳለ መረዳት የሚቻለው::

tg-me.com/ethiopianfacts/563
Create:
Last Update:

BY Amazing facts

Warning: Undefined variable $i in /var/www/tg-me/post.php on line 283

Share with your friend now:
tg-me.com/ethiopianfacts/563

View MORE
Open in Telegram

Amazing facts Telegram | DID YOU KNOW?

Date: |

Telegram hopes to raise $1bn with a convertible bond private placement

The super secure UAE-based Telegram messenger service, developed by Russian-born software icon Pavel Durov, is looking to raise $1bn through a bond placement to a limited number of investors from Russia, Europe, Asia and the Middle East, the Kommersant daily reported citing unnamed sources on February 18, 2021.The issue reportedly comprises exchange bonds that could be converted into equity in the messaging service that is currently 100% owned by Durov and his brother Nikolai.Kommersant reports that the price of the conversion would be at a 10% discount to a potential IPO should it happen within five years.The minimum bond placement is said to be set at $50mn, but could be lowered to $10mn. Five-year bonds could carry an annual coupon of 7-8%.

Mr. Durov launched Telegram in late 2013 with his brother, Nikolai, just months before he was pushed out of VK, the Russian social-media platform he founded. Mr. Durov pitched his new app—funded with the proceeds from the VK sale—less as a business than as a way for people to send messages while avoiding government surveillance and censorship.

Amazing facts from hk

Telegram Amazing facts
FROM USA